ኢትዮጵያ የተሳካ የኮሌራ ክትባት ዘመቻ አካሄደች በኢትዮጵያ የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር ከቅርብ ወራት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። በምላሹም በሀገሪቱ መጠነ ሰፊ የኮሌራ ክትባት ዘመቻ የተጀመረ ሲሆን ዘመቻው አሁን 98.4% ሽፋን (ከ10,196,575 ሰዎች በላይ) ደርሷል። የአፍ ኮሌራ የክትባት ዘመቻዎች በተጠቁ እና በአቅራቢያ በሚገኙ ወረዳዎች እየተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ቡድኖች የውሃ ደህንነትን ለማሻሻል እየሰሩ እና የአካባቢውን ህዝብ ስለ ንጽህና አጠባበቅ አስፈላጊነት እርምጃዎች በማስተማር ላይ ይገኛሉ። እ.አ.አ. በ2030 ኮሌራን ለማጥፋት በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ፍኖተ ካርታ መሰረት ኢትዮጵያ በሽታውን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት የዓለም ጤና ድርጅት አስፈላጊውን የቴክኒክ እውቀት፣ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል አቅርቧል። "በግጭት እና በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ፈተና ቢገጥመውም ዘመቻው በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራር እና በአጋር አካላት አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል" ሲሉ ዶ/ር ፓትሪክ አቦክ የዓለም ጤና ድርጅት የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ መሪ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia