" ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ " : አሜሪካዊው የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት ኢትዮጵያ በሰው ዘር ታሪክ ያላትን ሚና አረጋግጧል።

" ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ " : አሜሪካዊው የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት ኢትዮጵያ በሰው ዘር ታሪክ ያላትን ሚና አረጋግጧል።ታዋቂው የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን አውስትራሎፒተከስ ሉሲን በ1974 ዓ.ም ያገኙ ሲሆን፤ ሁሉም የሰው ልጆች ወደ መገኛቸውን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልፀው " ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ " የሚለው መፈክር ሙሉ በሙሉ ተገቢ ነው ብለዋል። ፕሮፌሰር ጆሃንሰን የሉሲን ቅሪተ አካል የተገኘበት 50ኛ አመት በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ላይ እንዳሉት የኢትዮጵያን የተገኘው አስደናቂ ቅሪተ አካል በሚሊዮን የሚቆጠር አመታት ያስቆጠረ መሆኑን ጠቁመዋል። “ኢትዮጵያ ከ 6ሚሊዮን ዓመታት በፊት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለው ጊዜ የሚያሳይ ቅሪተ አካል አላት። "ስለዚህ ኢትዮጵያ በጣም ጠቃሚ ሀገር ናት፤ ማን እንደሆንን፣ ከየት እንደመጣን እና በተፈጥሮ አለም ውስጥ ያለንን ቦታ እንድንረዳ ታደርገናለች" ሲሉ ተነገረዋል።እንደ ፕሮፌሰር ጆሃንሰን ንግግር ኢትዮጵያ በሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ውስጥ ካላት ሚና ባሻገር ያላትን ባህላዊና ታሪካዊ ጠቀሜታ አድንቀው ጎብኚዎች የተለያየ መልክዓ ምድሯን እና የበለጸጉ ቅርሶቿን እንዲጎበኙ አሳስበዋል። አዲስ የተመረቀውን የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የኢትዮጵያን ልዩ ታሪክ እና የፅናት ማሳያ አድርገው በመጥቀስ፤ ለኢትዮጵያውያንም ሆነ ለመላው አፍሪካ ጎብኚዎች ያለውን ጠቀሜታ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "ኢትዮጵያን በቱሪስትነት የሚጎበኝ ማንኛውም ሰው ሌላ ነገር ከማድረጉ በፊት ወደዚህ ሙዚየም መምጣት አለበት ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። "ሙዚየሙ በኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ብሎም በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ውብ፣ መረጃ ሰጭ ቦታዎች አንዱ ነው።" ብለዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik