የነሐሴ 1 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች ማሊ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ተያይዞ ኒጀር ከዩክሬን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነነት ማቋረጧን የሽግግር ምክር ቤቱ ተወካይ አስታወቀዋል። ሞስኮ በሩሲያ እና በኔቶ ሀገራት መካከል የእስረኞች ልውውጥን እንዲደረግ ለአንድ አመት ከ7 ወራት ያህል ጠብቃለች ሲሉ የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር (SVR) ገልፀው፤ ልውውጡ ለሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ጉልህ ሥፍራ የሚሰጠው ክስተት ነው ብለዋል ። የሩሲያ አየር መከላከያ ሰራዊት በቤልጎሮድ፣ ኩርስክ፣ ቮሮኔዝ እና ሮስቶቭ ክልሎች ላይ በአንድ ጀምበር 11 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማውድውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። የአሜሪካ ወታደራዊ ኮንትራክተሮች ወታደራዊ ጦር መሳሪያዎችን ከዩክሬን ጋራ ለማምረት የሚያስችል ውል ለመፈራረም የሚያስቸኩል ነገር የለም ማለታቸውን የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፍልስጤም በሰላም ኮንፈረንስ ማዕቀፍ ውስጥ በመጨረሻው ሁኔታ ላይ ከእስራኤል ጋር ላይ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ገለፁ። የሩሲያ እና የኢንዶኔዢያ መርከበኞች በጃቫ ለመጀመሪያ ጊዜ የሁለትዮሽ ልምምዶችን እ.አ.አ ከህዳር 4-8 እንደሚያደርጉ የኢንዶኔዥያ ጦር ሃይሎች አዛዥ አስታወቁ።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia