በኦሎምፒክ መንደር የሚቀረበው ምግብ ውስጥ ትሎች እንደተገኙ የሶስት ጊዜ የኦሎምፒክ የዋና ስፖርት ውድድር ሻምፒዮኑ ተናገረየብሪታኒያው የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት አዳም ፒቲ በፓሪስ 2024 አዘጋጆች፤ በኦሎምፒክ ውድድር መስተንግዶ ላይ በቂ ምግብ ባለማግኘቱ መቸገሩን ተናግሯል።" የአስተማማኝ አቅርቦት ትርክት በአትሌቶች ዘንድ አልሰራም። ውድድሬን በብቃት ለማከናወን ስጋ መብላት እፈልጋለሁ፤ ሀገሬም እያለሁ ስጋ ነውየምበላው፤ ስለዚህ ለምን እዚህ ሲሆን ሌላ ምግብ ለመብላት እገደዳለሁ? " ሲል ፔቲ ጥያቄ አቅርቧል።"እኔ አሳ መመገብ እወዳለሁ ነገር ግን ሰዎች በአሳው ውስጥ ትሎች እያገኙ ነው፤ ያ ጥሩ አይደለም" ሲል ሃሣቡን አጠቃሏል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia