ደቡብ አፍሪካ ለዩክሬን ሰላም የደቡባዊ ዓለም ቅንጅትን ለማሳደግ ቃል መግባቷን ቤጂንግ አስታወቀች "ደቡብ አፍሪካ የቻይናን 'ሸትል ዲፕሎማሲ' በጣም እንደምታደንቅ እና የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ትብብራቸውን በማጠናከርና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የእውነት እና ፍትህ ድምጽ በመሆን ግጭትን የሚያበርዱ እና ሰላምን የሚያሰፍኑ ሁኔታዎች መፈጠር አንዳለባቸው ገልጻለች" ሲል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ተናግሯል። እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ የቻይና መንግሥት የዩሬዥያ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሊ ሁይ አርብ እለት ደቡብ አፍሪካን በጎበኙበት ወቅት ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው በዩክሬን ቀውስ ዙርያ ተወያይተዋል። ለዩክሬን ቀውስ ፖለቲካዊ እልባት ለመፈለግ በቻይና እና ብራዚል መኻከል የተደረሰው ባለ ስድስት ነጥብ ስምምነት ከ110 በላይ ሀገራት አዎንታዊ አስተያየት ማግኘቱንም ጠቁሟል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia