ፀረ-ሩሲያ ማዕቀቦች በአፍሪካ የእህል አቅርቦት ላይ ተጽእኖ ማሳደራቸውን እና እጥረቱን እንዳባባሱ የተመድ ባለሙያ ተናገሩ በተመድ የአንድ ወገን አስገዳጅ እርምጃዎች የሰብዓዊ መብቶች ተጠቃሚነት ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተፅእኖ የሚመረምሩት ልዩ ዘጋቢ ኤሌና ዶቭጋን ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "የአንድ ወገን አስገዳጅ እርምጃዎች የዓለም የምግብ ገበያን እንዳፈራረሰ እንዲሁም እያደጉ ባሉ ሀገራት ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን" ተናግረዋል። "በሩሲያ ላይ የተጣለው የአንድ ወገን ማዕቀብ በአፍሪካ ሀገራት የእህል አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፤ ይህም በእነዚህ ሀገራት ቀድሞም የነበረውን አስቸጋሪ የሰብዓዊ ሁኔታ እንዲባባስ አስተዋጽኦ አድርጓል። የአንድ ወገን አስገዳጅ እርምጃው በተወሰደባቸው ሀገራት የምግብ ዋስትና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል" ሲሉም አብራርተዋል። የአንድ ወገን ማዕቀቡ ማዳበሪያ፣ የከብት ክትባት እና ዘር ለማግኘት እንቅፋት እንደሆነ እና "ይህም የምግብ ዋስትናን በእጅጉ እንደጎዳ" ባለሙያው ገልጸዋል። "የመጀመሪያ የክትትል ውጤቶች የአንድ ወገን ማዕቀቡ በአብዛኞቹ ሀገራት የምግብ ዋጋ ግሽበትን እንዳስከተለ አሳይተዋል…በአንድ ወገን አስገዳጅ እርምጃዎቹ ትግበራ ምክንያት በአፍጋኒስታን፣ ክሮኤሺያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ዚምባብዌ፣ ቻይና፣ ማሊ፣ ኒካራጓ፣ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና፣ ቤላሩስ እና ኢራን ውስጥ የምግብ ዋጋ መዋዠቅ ጠቋሚ ምልክቶች እንደተመዘገቡ" ኤክስፐርቱ ተናግረዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በዚህ ጉዳይ ሞስኮ ተጠያቂ ናት በማለት ዋሽንግተን ክስ ብታቀርብም ለዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና መፈራረስ ተጠያቂዎቹ ምዕራባውያን ናቸው ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia