የሐምሌ 26 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 እስራኤል ራሷን ከኢራን መከላከል እንድትችል ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ የጦር ጀቶችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንደምትልክ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 ዩክሬን 13,570 ወታደሮችን ባለፈው ሳምንት እንዳጣች የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 በናይጄሪያ የፀረ-መንግስት ተቃውሞ መቀጠሉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 በሩሲያ ኒዝሂ ታጊል በደረሰው የጋዝ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ሰባት መድረሱንና የነፍስ አድን ሰራተኞች የተጨማሪ አንድ ሰው አስከሬን ከፍርስራሽ ማውጣታቸውን የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ። የሶስት ሰዎች እጣ ፈንታ እስካሁን እንዳልታወቀና የፍለጋ እና ማዳን ስራ እንደቀጠለ ተገልጿል። 🟠 በኦሎምፒክ ድርብ ውድድር ለፍጻሜ የደረሱት የሩሲያ የቴኒስ ተጨዋቾች ሚራ አንድሬቫ እና ዲያና ሽኔይደር በጨዋታው ሜዳሊያ እንደሚያገኙ አረጋግጠዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia