ማሌዢያ ብሪክስን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት ደቡብ አፍሪካ ድጋፍ እንድታደርግ ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

ማሌዢያ ብሪክስን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት ደቡብ አፍሪካ ድጋፍ እንድታደርግ ፍላጎት እንዳላት ገለጸች የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም እና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ትናንት ሐሙስ ውይይት አካሂደዋል። ከተወያዩባቸው ርእሰ ጉዳዮች አንዱ ማሌዢያ የብሪክስ አባል የመሆን እድሏን የተመለከተ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ "በተጨማሪም የደቡባዊ ዓለም ታዳጊ ሀገራት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን እና መጠናከር ስላለባቸው ትብብሮች አንስቻለሁ" ብለዋል። የሩሲያ የላይኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቫለንቲና ማቲቪንኮ 24 ሀገራት የብሪክስ ቡድንን ለመቀላቀል እየተጠባበቁ እንደሆነ ሐምሌ ወር ላይ አስታውቀዋል። ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እ.አ.አ ጥር 1 ቀን 2024 የብሪክስ ሙሉ አባል በመሆን ተቀላቅለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik