የዩክሬን ጦር በሳምንቱ በአጠቃላይ እስከ 13,570 የሚደርሱ ወታደሮችን እንዳጣ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ የሩሲያ ጦር ዩክሬን በሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት ላይ አልሞ ተኳሽ የጦር መሳሪዎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ተጠቅሞ 11 ጥቃቶችን ባለፈው ሳምንት እንዳካሄደ ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል። እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ በጥቃቱ ታጠቂ ተሽከርካሪዎችን፣ የመገጣጠሚያ ፋብሪካዎችን፣ የድሮን ማከማቻ መጋዝኖችን እና የጥይት ግምጃ ቤቶችን የሚገጣጠሙ እና የሚጠግኑ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም የቅጥረኞች ማሰማሪያ ቦታዎችን መቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia