የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ቱዋዴራ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሉዋ በሀገሪቱ ላይ ተጥሎ የቆየውን የጦር መሳሪያ እገዳ መነሳት ከህዝቡ ጋር አከበሩ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በ2013 በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ ጥሎት የነበረውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ እገዳ እ.አ.አ. ሐምሌ 30 ቀን አንስቷል። በሀገሪቱ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የተቀመጠው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ክልከላ ባለበት ይቀጥላል። የማዕከላዊ አፍሪካ ዲፕሎማቶች ውሳኔውን “የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን እና የሕዝቦቿን ክብር የመለሰ ታሪካዊ ምዕራፍ” ሲሉ አወድሰውታል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia