ማሌዥያ ብሪክስን ለመቀላቀል ለሩሲያ የማመልከቻ ደብዳቤ አቀረበች የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም "ማሌዢያ በብሪክስ ድርጅት በአባልነት ወይም በስትራቴጂክ አጋርነት ከመሳተፍ ባለፈ ብሪክስን ለመቀላቀል ለድርጅቱ ሊቀመንበር ሩሲያ ማመልከቻ አቅርባለች" ማለታቸውን አንስቶ የመንግስት የዜና ወኬል በርናማ ዘግቧል። ማሌዢያ ብሪክስን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት በእስያዊቷ ሀገር ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር የተነጋገሩበት ዋና ርዕሰ ጉዳይ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia