ሩሲያ ማሌዢያ በዩክሬን ግጭት ዙርያ የያዘችውን ሚዛናዊ አቋም አወደሰች የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከማሌዢያ ጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ስለ ዩክሬን ተነጋግረናል። ምእራባውያኑ ዩክሬንን ኔቶ ውስጥ በመሳብ ወደ ፀረ-ሩሲያ ህብረት ለመቀየር ያደረጉት ሙከራ የዚህ ቀውስ መንስኤ መሆኑን በመረዳት ለያዙት ሚዛናዊ እና ያልተዛባ አቋም ለማሌዢያ ባልደረቦቻችን ምስጋናችንን ገልፀናል" ብለዋል። ስለ ምዕራባውያን የተናገሩት ዲፕሎማቱ የአሜሪካ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በደቡብ ምስራቅ እስያ ሊሰማራ የሚችልበት ሁኔታ የአካባቢውን የጸጥታ ስጋት እንደሚጨምር አስታውቀዋል። አሜሪካውያን ከረጅም ጊዜ በፊት የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቻቸውን ለኔቶ አጋሮቻቸው እንዳጋሩም አስታውሰዋል። "ይህንን 'የጋራ የኒውክሌር ተልእኮ' ይሉታል በዚህም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ያለሆኑ ሀገራት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ስልጠና የሚወስዱበት ነው" ሲሉ ላቭሮቭ አብራርተዋል። በቀጠናው ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ የውጫዊ ሀይሎች ከሚወስዱት “እብሪተኛ” ድርጊት አንፃር ሩሲያ የማረጋጋት ሚና የመጫወት እድል እንዳለት የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ይገነዘባሉ ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia