የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ እርሻ የተላከ ድንች ደረሳቸው በሐምሌ ወር መጀመሪያ ቤላሩስን የጎብኙት ኦክሲሊያ ምናንጋግዋ ከሉካሼንኮ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህ ሳምንት መገባደጃ የቤላሩስ ሴቶች ህብረት የልዑካን ቡድን በቀዳማዊት እመቤቷ ግብዣ ዚምባብዌን ጎብኝቶ በአፍሪካ ሴቶች ፎረም ላይ ተሳትፏል። "ከሚንስክ እስከ ዚምባብዌ ቪክቶሪያ ፏፏቴ ድረስ ከስድስት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘው እጅግ ዋጋ ያለው ጭነት ዛሬ ለተቀባዩ ደርሷል- ከቤላሩስ መሪ እርሻ የተላከ ድንች ለቀዳማዊት እመቤት ተላልፏል። ኦክሲሊያ ምናንጋግዋ ቤላሩስን በጎበኙበት ወቅት በጣም የወደዷቸው 'ፐርሻትስቬት' እና 'ማኒፌስት' የተባሉ ታዋቂ ዝርያዎች ናቸው" ሲሉ የቤላሩስ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአዲሱ ሰብል ድንቾች በሁለት ልዩ የእንጨት ሳጥኖች ውስጥ እንደደረሱ ዘገባው አመላክቷል። ድንቾቹ ለመብል እንደሚሆኑ እና ለተክል የሚሆኑ የድንች ዘሮች በቅርቡ ወደ ዚምባብዌ እንደሚላኩ ተገልጿል። ቀዳማዊት እመቤቷ በበኩላቸው ዚምባብዌ ውስጥ የሚተዋወቀው የቤላሩስ ድንች በጥሩ ሁኔታ ይበቅላል የሚል እምነታቸውን ገልጸዋል። ለጨዋታም የድንች ዝርያው ዚምባቡዌ ነው ወይስ ቤላሩስ የተሻለ የሚያድገው ብለው ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮን ውርርድ ገጥመዋል። ከቤላሩስ የግብርና ምርቶች በተጨማሪ ዚምባብዌ የቤላሩስ የቤት ዕቃዎችን፣ ቀላል የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የእንግዳ መስተንግዶ ኢንዱስትሪ መዋቢያዎችን እንደምትፈልግ የቤላሩስ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia