የብሪክስ ሙፍቲዎች ሩሲያ ካዛን በተካሄደው ፎረም መንፈሳዊ ውይይት አካሄዱ ለመንፈሳዊ የሲልክ ሮድ መድረክ በካዛን የተሰባሰቡ የብሪክስ ሙፍቲዎች ሐይማኖታዊ ውይይቶችን በድርጅቱ ማዕቀፍ ውስጥ ለማስፋት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። የቁርዓን ንባብ ውድድርን ባካተተው ፎረም ከሩሲያ ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፣ ኢራን ፣ ግብፅ ፣ ቻይና ፣ ብራዚል ፣ ኢትዮጵያ ፣ ህንድ እና ከደቡብ አፍሪካ የመጡ የሐይማኖት መሪዎች የትብብር ሰነድ ፈርመዋል። ይህ ትብብር መንፈሳዊ እና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን እንዲሁም የቤተሰብ እሴቶችን መጠበቅ፣ ትውልድ ሀገርን መውደድ እና ጽንፈኝነትን እና ሽብርተኝነትን መቃወም ላይ ያተኩራል። ከብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ በፊት የተካሄደው የፊርማ ስነ-ስርዓት የሐይማኖት መሪዎቹ ለአባል ሀገራቱ መሪዎች ያደረጉት ምርቃት እንደሆነ ተቆጥሯል። ሐይማኖታዊ ውይይት እና መግባባትን ለማበረታታት ያለመውን መንፈሳዊ የሲልክ ሮድ ፕሮጀክት የብሪክስ ሃገራት የሙስሊም ማህበረሰብ ተሳታፊዎች አወድሰውታል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia