ቻይና በዩክሬን ቀውስ የአሜሪካን ጫና እንደማትታገስ አሰታወቀች የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከአሜሪካ አቻቸው አንቶኒ ብሊንከን ጋር ባደረጉት ውይይት "ግፊት ወይም ማስፈራሪያን አንታገስም መሰረታዊ ጥቅሞቻችንን እና ህጋዊ መብቶቻችንን ለማስጠበቅ የማያወላዳ እና ፍቱን እርምጃዎችን እንወስዳለን" ብለዋል። ቻይና በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያላት አቋም ግልፅ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ቤጂንግ ሰላምና ድርድርን ማበረታታት እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ዲፕሎማቱ አሜሪካ የአንድ ወገን ማዕቀብ መጣል እና "ረጅም ክንድ ስልጣን" (ህግን ከግዛት ውጭ ስራ ላይ ማዋል) ያለ ልዩነት መጠቀሟን ማቆም አለባት ሲሉም አሳስበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia