የሐምሌ 19 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የሩሲያ ኤስ.ዩ-27 የጦር ጀት አር.ሲ-135 የስለላ አውሮፕላን እና ሁለት የብሪታኒያ አየር ሃይል ታይፉን ተዋጊዎች በጥቁር ባህር ላይ መታየታቸውን ተከትሎ የተጠንቀቅ ትዕዛዝ እንደተሰጠው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የአሜሪካ እና የእንግሊዝ አውሮፕላኖች በየመን የሁቲ ቦታዎች ላይ አርብ ዕለት አዲስ ጥቃት ማድረሳቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ለስፑትኒክ ተናገሩ። 🟠 የአውሮፓ ህብረት ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች ከተገኘ ገቢ 1.5 ቢሊዮን ዩሮ ወደ ዩክሬን እንደሚልክ የህብረቱ ኮሚሽን አስታወቀ። 🟠 ዩቲዩብ 200 የሩሲያ ቻናሎችን ማገዱን ከነዚህም ውስጥ 80 የሚሆኑት በያዝነው ዓመት እንደሆነ የሩሲያ የመረጃ ተቆጣጣሪ ገለጸ። 🟠 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ቀዳማዊት እመቤት ባራክ እና ሚሼል ኦባማ የካማላ ሃሪስን የምርጫ ፉክክር እጩነት እንደሚደግፉ ተናግረው እንድታሸንፍ የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia