ሩሲያ ወደ አፍሪካ የምትልከው የፔትሮሊየም ምርት በ2023 በ3.5 እጥፍ ጨመረ በዚህም ምክንያት ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች መጠን 17.6 ሚሊዮን ቶን መድረሱን የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር ኃላፊ ዲሚትሪ ሴሚዮኖቭ ሐምሌ 18 ቀን ተናግረዋል። ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የሚደረጉ የኢነርጂ ትብብር ፕሮጀክት ውይይቶች በ2022 ከነበረው 30 አሁን ወደ 40 ከፍ ብሏል። 14 የአፍሪካ ሀገራት "ቅድሚያ የሚሰጣቸው" እንደሆኑ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። "የእኛ ኩባንያዎች በአህጉሪቱ በስፋት ተወክለዋል። ይህ በነዳጅ እና ጋዝ ዘርፍ በምርት እና ትራንስፖርት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችንም ያጠቃልላል" ብለዋል ኃላፊው። በተጨማሪም ሩሲያ በአፍሪካ ሀገራት የኢነርጂ ዘርፍ የጋዝ አጠቃቀምን ለማስፋት እና ጋዝን እንደ ሞተር ነዳጅ ለመጠቀም ትፈልጋለች። በኤሌክትሪክ መስክ እና በአማራጭ ኃይል ዙርያ እንደ የፀሐይ እና የንፋስ ኃይል ፕሮጀክቶችም በሀሳብ ደረጃ ቀርበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia