ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ሴት ዋና ዳኛ በመሾም ታሪክ ሰራች የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ማንዲሳ ማያን የሀገሪቱ የመጀመሪያ ሴት ዋና ዳኛ አድርገው የሾሙ ሲሆን በፍትህ ስርዓቱ የፆታ እኩልነትን ለማምጣት ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት ምክትል ዋና ዳኛ የሆኑት ማያ የስራ ጊዜያቸውን እያገባደዱ ያሉትን ሬይሞንድ ዞንዶን በመተካት ነሐሴ 26 አዲሱን ሃላፊነት ይረከባሉ። ሹመቱ ከዳኝነት አገልግሎት ኮሚሽን ጋር ምክክር ከተደረገ በኋላ እንደተወሰነ የገለፁት ራማፎሳ ማያ በቦታው መመደባቸው የሚኖረውን ታሪካዊ ትርጉም ግምት ውስጥ በማስገባት ኮሚሽኑ እንደመረጣቸው ተናግረዋል።ማያ ቀደም ሲል በደቡብ አፍሪካ ሁለተኛውን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ችሎት በፕሬዝዳንትነት በማገልገል ሃላፊነቱን የያዙ የመጀመርያው ጥቁር ሴት መሆን ችለዋል። በበርካታ ሀላፊነቶች የመጀመርያ በመሆን የስራ ዘመናቸው የሚገለፀው ዳኛ ማያ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እና በፕሬዝዳንትነት በመምራትም የመጀመሪያዋ ሴት ናቸው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia