የአፍሪካ ሀገራት ከምዕራቡ ዓለም ጋር ግንኙነት መፍጠር ላይ ያላቸው አመለካከት በከፍተኛ ደረጃ እየተቀየረ ነው ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረየሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ አምባሳደር እና የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም ሴክሬታሪያት ኃላፊ ኦሌግ ኦዜሮቭ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በኢነርጂ ዘርፍ የኢኮኖሚ ትብብር ለመፍጠር የህግ አውጭዎች ድጋፍን አስመልክቶ በተካሄደው ስትራቴጂካዊ ስብሰባ ላይ የተናገሩት ነው። አፍሪካ ከሞስኮ ጋር ያላት ግንኙነትም እየተቀየረ መምጣቱን ዲፕሎማቱ ጠቁመዋል። "አፍሪካ እንደ እንግሊዘኛ እና ፈረንሣይኛ ያሉትን 'የኢምፔሪያሊስት' ቋንቋዎችን በመተው በራሷ ድምጽ መናገር ጀምራለች። የአፍሪካ አህጉር ግዙፍ ብሔራዊ እና የስልጣኔ መነቃቃት ሂደትን ጀምሯል" ሲሉ ኦዜሮቭ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia