የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አስታወቁ
ቀጣዩ የቱኒዚያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መስከረም 26 ይካሄዳል።
ከ2019 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙት ካይስ ሰይድ ጽህፈት ቤታቸው በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ባስተላለፉት መልእክት "መስከረም 26 ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ መሆኔን በይፋ አስታውቃለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
ሰይድ እ.አ.አ ሐምሌ 25፣ 2021 የኑሮ ሁኔታ መባባሱን ተከትሎ በፓርላማ እና በቱኒዚያ እስላማዊ ፓርቲ ኢናህዳ ላይ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት መንግስትን በትነው ፓርላማውን አግደዋል። ፕሬዝዳንቱ “መንግስትን እና ተቋማቱን ለመጠበቅ” ፓርላማውን እንዳሰናበቱ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia