ባይደን የህዳሩን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደማያሸንፉ እንደተቀበሉና ከውድድሩ ሊወጡ እንደሚችሉ ተዘገበ
ኒውዮርክ ታይምስ ለባይደን ቅርብ የሆኑ አንድ ሰው ጠቅሶ ሐሙስ ዕለት እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ከፉክክሩ ለመውጣት ገና አልወሰኑም።
ሆኖም ጋዜጣው ያጣቀሳቸው ሌላ ምንጭ “እውነታው እየገባቸው” እና ባይደን በቅርቡ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስን ምትካቸው አድረገው እንደመረጡ ቢያስታውቁ ምንም አያስደንቅም ብለዋል።
በተመሳሳይ ጋዜጣው የዋይት ሀውስ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ባይደን ከውድድሩ አይወጡም ብሏል። በባይደን ላይ ያለውን ጫና ለማባባስ በዲሞክራት ፓርቲ መሪዎች የተቀነባበረ የውሸት ዘመቻ ነው በማለት የመገናኛ ብዙሃኑን ዘገባ ውድቅ አድርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia