የሐምሌ 11 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
🟠 አሜሪካ የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን በጀርመን የምታሰማራ ከሆነ ሞስኮ ተመሳሳይ የኒውክሌር አቅም ያላቸው ስርዓቶችን ልታሰማራ እንደምትችል የሩሲያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪያብኮቭ ገለፁ።
🟠 በሩሲያ ቤልጎሮድ ክልል ኦትራድኖዬ በተባለ መንደር የዩክሬን ጦር አንድ መኪና ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ሶስት ሰዎች እንደቆሰሉ የአካባቢው አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
🟠 አሜሪካ ከኒውዮርኩ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ከላቭሮቭ ጋር ውይይት እንዳልጠየቀች የሩሲያ የዲፕሎማሲ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
🟠 በርካታ ከፍተኛ የዲሞክራት ፓርቲ አመራሮች ፕሬዝዳንት ባይደን በሳምንቱ መጨረሻ ከመጪው ፕሬዝዳንታዊ ፉክክር ለመውጣት ይገደዳሉ ብለው እንደሚጠበቁ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
🟠 ቢያንስ 401 ህግ አውጪዎች ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽንን በድጋሚ እንዲመሩ የመረጡ ሲሆን 284ቱ ሲቃወሙ 15ቱ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
🟠 ባንግላዲሽ ውስጥ በተቀሰቀሰ ሁከት በትንሹ 11 ሰዎች ሲገደሉ ከ500 በላይ መቁሰላቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
🟠 የፈረንሳይ ፖሊሶች ለ"ፈረንሳይ ገፅታ" ሲባል በመጪው ኦሊምፒክ በስራ ላይ ማስቲካ እንዳያኝኩ ተከለከሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia