የሐምሌ 11 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
🟠 ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሳዑዲ አልጋወራሽ ሞሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በስልክ ተወያይተው የኦፔክ+ ውህደትን ጨምሮ በሃይል እና በሌሎች ትብብሮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
🟠 የሩሲያ አየር መከላከያዎች በክራይሚያ ልሳነ ምድር 33 እንዲሁም በብራያንስክ ክልል 2 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በአንድ ሌሊት ሲያጨናግፉ 10 ሰው አልባ ጀልባዎችን ጥቁር ባህር ላይ ማውደማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
🟠 ዋይት ሀውስ ጆ ባይደን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አረጋገጠ፡፡ ነገር ግን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ክትባት እንደወሰዱ እና ቀለል ያሉ ምልክቶች እንደሚታይባቸው ገልጿል።
🟠 ዶናልድ ትራምፕ ሐምሌ 11 አመሻሽ ሚልዋኪ እየተካሄደ በሚገኘው የሪፐብሊካን ፓርቲ ኮንቬንሽን የመዝግያ ንግግር እንደሚያደርጉና የፓርቲው ፕሬዝዳንታዊ እጩነታቸውን በይፋ ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
🟠 ትራምፕ ላይ የተኮሰው ቶማስ ማቲው ክሩክስ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ላይ የግድያ ሙከራ ከማድረጉ በፊት በቪድዮ ጨዋታ መድረክ ላይ መልእክት እንዳስተላለፈ እና ለእሳቸው አንድ ዓይነት “ትርኢት” ሐምሌ 6 እንደሚከናወን መግለፁን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia