በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ትራምፕ ላይ ስለተደረገው የግድያ ሙከራ እስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች

በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ትራምፕ ላይ ስለተደረገው የግድያ ሙከራ እስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች ▪ ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የትራምፕ ረዳቶች ተናግረዋል። ▪ የህግ አስከባሪ ባለስልጣናት በትራምፕ የግድያ ሙከራ ዙሪያ ለባይደን ማብራሪያ ሰጥተዋል። ▪ ባይደን በፔንስልቬንያ በተደረገው የትራምፕ የድጋፍ ሰልፍ ወቅት የነበረውን የደህንነት እርምጃዎችን በሙሉ እንዲገመገም ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ▪ የመገናኛ ብዙሃን ምንጮችን ጠቅሰው እንደተናገሩት የግድያ ሙከራ ያደረገው ግለሰብ ከአክራሪ ድርጅቶች አልያም "ትልቅ ሴራ" ስለመኖሩ የተገኘ ፍንጭ አለመኖሩን ገልጸዋል። ▪ ተኳሹ የተጠቀመበት ሽጉጥ አባቱ በህጋዊ መንገድ የገዛው እንደሆነ ተገልጿል። ▪ ተጠርጣሪው ቶማስ ማቲው ክሩክስ በትምህርት ቤት ውስጥ " ዝምተኛ ልጅ" እንደነበር እና ብዙ ጓደኞች ያልነበሩት እንደነበር ተገልጿል። ▪ የ20 አመቱ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ሪፐብሊካን እንደነበረ የፔንስልቬንያ የመራጮች መዛግብት አመላክቷል። ▪ በተጠርጣሪው ቤት እና መኪና ውስጥ ፈንጂ የሚሠሩ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል። ▪ የአካባቢው ፖሊሶች እና የአይን እማኞች ከድጋፍ ሠልፉ በፊት ተኩስ የከፈተው ግለሰብ ላይ አጠራጣሪ ባህሪ ተመልክተው መረጃውን ለደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች ሪፖርት አድርገው ነበር። ▪ የፔንስልቬንያ የድጋፍ ሰልፍ ታዳሚዎች የግድያ ሙከራው እንዲፈጸም የፈቀዱት የደህንነት አባላት ባሳዩት “የደህንነት ሥነ ምግባር መጣስ” አስደንግጧቸዋል። ▪ ተጠርጣሪው የተኮሰበት ጣሪያ የምርጫ ቅስቀሳ ዝግጅቱ ከመደረጉ ቀደም ብሎ ፍተሻ ተደርጎ እንደነበር ተገልጿል። ▪ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የሪፐብሊካን አባል የሀገሪቱን የሀገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ የትራምፕን ደህንነት ለማስጠበቅ ፈቃደኛ አልሆነም ሲሉ ከሰዋል። ▪ የትራምፕ የደህንነት ጥበቃ እንዲጨምር የቀረበለት ጥያቄ መኖሩን የአሜሪካው ደህንነት አገልግሎት ውድቅ አድርጓል። ▪ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ሰራተኞች እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ እና ዌስት ፓልም ቢች ያሉ ቢሮዎችን እንዳይሄዱ ተነግሯቸዋል፤ ምክንያቱም የደህንነት ፍተሻዎች መደረግ ስላለበት እንደሆነ ተነግሯል። ▪ እ.አ.አ ከሐምሌ15-18 የሚካሄደው የሪፐብሊካን ብሔራዊ ኮንቬንሽን የጸጥታ እቅድ እየተከለሰ ነው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik