በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በመኪና ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ በትንሹ 10 ሰዎች ሞቱ
ሆርን ኦብዘርቨር የህግ አስከባሪ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው 20 ሰዎች መቁሰላቸውን እና የሟቾቹም ቁጥር ከተጠቀሰው በላይ ሊጨምር እንደሚችል ገልጿል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በሞቃዲሾ በሚገኝ እና በርካታ ሰዎች በሚበዙበት ካፌ ውስጥ ሲሆን ድርጊቱ በአጥፍቶ ጠፊ የተፈጸመ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ደንበኞች የዩሮ 2024 የእግር ኳስ ፍፃሜ ጨዋታን ለመመልከት በቶፕ ቡና ካፌ ተሰብሰበው እንደነበር የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ለፕሬዝዳንቱ ቤተ-መንግስት ቅርብ የሆነውን አካባቢ በመሆኑ ፖሊስ መንገዱን ዘግቶታል።
ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።
ምስሎቹ ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ናቸው
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia