በናይሮቢ ምስጢራዊ ግድያ የተሳተፉት አካላት በህግ እንደሚጠየቁ የኬንያው ፕሬዝዳንት ቃል ገቡ።

በናይሮቢ ምስጢራዊ ግድያ የተሳተፉት አካላት በህግ እንደሚጠየቁ የኬንያው ፕሬዝዳንት ቃል ገቡ። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዋና ከተማይቱ ናይሮቢ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሙኩሩ ውስጥ በሚገኝ መንደር ውስጥ በሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ስፍራ ተገድለው የተገኙት የዘጠኝ ሴቶች አስመልክተው ያላቸውን ከፍተኛ ስጋ ገልፀዋል። "ኬንያውያን ወጣት ልጃገረዶችን ጨምሮ ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ጉዳይ በፍጥነት መጣራት አለበት፣ እናም በዚህ አፀያፊ ተግባር የተሳተፉ አካላት እንዲቀጡ፣ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እና ህጉም ሙሉ ለሙሉ መተግበር ይኖርበታል" ብለዋል ሩቶ። የኬንያ ፖሊስ ግድያውን ከአምልኮ ሥርዓት፣ ከተከታታይ ግድያዎች እና ከህክምና ባለሙያዎች ማጭበር ጋር ሊኖር የሚችለውን ግንኙነት እያጣራ መሆኑን ገልጿል። ተጎጂዎቹ በጆንያ እና በጥቁር ፖሊ ከረጢቶች የተጠቀለሉ እና በገመድ የታሰሩ ሲሆን አንዳንዶቹም ደግሞ ቃጠሎ የደረሰባቸው እና የመበስበስ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ መሆናቸው ተገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik