በሞዛምቢክ የሚገኘው የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ(ሳዲክ) የሰላም ተልዕኮ ነገ ሰኞ እንደሚያበቃ የዛምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አስታወቁ
ሙላምቦ ሀይምቤ ይህን ያሉት የሳዲክ የፖለቲካ፣የመከላከያ እና የደህንነት ጉዳዮች የሚኒስትሮች ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ባካሄዱት 26ኛው ስብሰባ ላይ ነው።
" ሃይምቤ እንደገለጹት በሞዛምቢክ የሚገኘው የሳዲክ ወታደራዊ ተልእኮ እ.ኤ.አ ሀምሌ 15 ቀን 2024 ከፔምባ ካቦ ዴልጋዶ ግዛት ሙሉ በሙሉ ለቆ እንደሚወጣ የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
እ.ኤ.አ በ 2021 በሞዛምቢክ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ወታደራዊ ተልእኮ በነዳጅ ዘይት ወደ በለፀገችው ካቦ ዴልጋዶ ግዛት በመዝመት፤የአማፂ ቡድኑን እንቅስቃሴ ለመግታት ያለመ ነበር። የሳዲክ ተልዕኮ ከቦትስዋና፣ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ከሌሴቶ፣ከማላዊ፣ከደቡብ አፍሪካ፣ ከታንዛኒያ እና ከዛምቢክ የተውጣጡ ወታደሮችን ያካተተ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia