የሐምሌ 04 የምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፡-
🟠 በማሊ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ማህበራት እንቅስቃሴ እንደገና እንደጀመረ የሳህል ሀገራት ጥምረት አስታውቋል፡፡
🟠 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የመንግሥታቸውን መበተን ገለፁ።
🟠 ቭላድሚር ፑቲን ከኢራን እስላማዊ አማካሪ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሞሀመድ ባገር ጋሊባፍ ጋር ተወያይተዋል። በተመሳሳይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ከታንዛኒያ የልዑካን ቡድን መሪ የታንዛኒያ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቱሊያ አክሰን ጋር በብሪክስ የፓርላማ መድረክ ላይ ተገናኝተዋል።
🟠 የዩክሬን ጦር በሩሲያ ቤልጎሮድ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ካሚካዜ ድሮኖችን በመጠቀም ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ሁለት ሹፌሮች እንደተጎዱ የክልሉ አስተዳዳሪ ቭያቼስላቭ ግላድኮቭ ገልጸዋል።
🟠 የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በኔቶ የመሪዎች ጉባኤ ባይደንን ላለማግኘት ይሸሹ እንደነበርና ከአሜሪካው መሪ ጋር የሁለትዮሽ ግኑኝነት አለመጠየቃቸውን ሶስት ምንጮች ለጋርዲያን ተናግረዋል።
🟠 ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ፖላንድ ከ1,000 ኪሎ ሜትር በላይ የሚወነጨፉ ክሩዝ ሚሳኤሎችን የማምረት እቅድ አላቸው ሲል ፋዝ የተሰኘው የጀርመን እትም አስነብቧል።
🟠 ካናዳ ለኪየቭ 367 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ እና ተጨማሪ የF-16 አብራሪዎችን እንደምታሰለጥን ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በኤክስ የትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ዴሞክራቶች የቀድሞው የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ባይደን ከፕሬዝዳንታዊ ፉክክሩ እራሳቸውን እንዲያገሉ ሊያሳምኑ ይችላሉ ብለው ያምናሉ ሲሉ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ጽፈዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia