ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ እያደረገች ነው
በቅርቡ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያ ውጤታማ ተሳትፎ እንዳደረገች በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በሙያተኞችና ሚኒስትሮች ደረጃ የምታደርገው ተሳትፎ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ብሪክስን የሚያጠናክር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በብሪክስ እያደረገች ያለው ተሳትፎ በትብብር ማዕቀፉ ለጋራ እድገት መረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል።
እንደ አምባሳደሩ ገለፃ አባል ሀገራቱ በሚቀይሱት የትብብር አቅጣጫ መሠረት ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች አጋርነቷን ታጠናክራለች።
ኢትዮጵያ የብሪክስ የልማት ባንክ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ሩሲያ እንደምትደግፍም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia