የሐምሌ 03 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

የሐምሌ 03 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 ኔቶ አደጋዎችን ለመከላከል እና ውጥረት ለመቀነስ ከሞስኮ ጋር የግንኙነት መስመሮችን መቀጠል ይፈልጋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። ይህንን የሚመለከት አንቀጽ በህብረቱ ጉባኤ ረቂቅ መግለጫ ውስጥ ተካትቷል። 🟠 አሜሪካ እና አጋሮቿ ወደ ዩክሬን የላኳቸው ኤፍ-16 ተዋጊ ጀቶች በዚህ ክረምት ኪዬቭ እንደሚደርሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ተናግረዋል። 🟠 አሜሪካ በ2026 የረዥም ርቀት መሳሪያዎችን በጀርመን ማሰማራት እንደምትጀምር ፔንታጎን አስታወቀ። 🟠 የዩክሬን የኔቶ አባልነት በህብረቱ እና በሩሲያ መካከል ቀጥተኛ ግጭት ስለሚፈጠር ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም ሲሉ የሃንጋሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲጃርቶ ተናግረዋል። 🟠 የብሪክስ እንቅስቃሴ ዩናይትድ ስቴትስን ያናድዳል፤ በሀገራት ላይ ጫና ለመፍጠር ይሞክራሉ ነገር ግን የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ግንባታ ሂደት ሊቆም አይችልም ሲሉ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ቫለንቲና ማትቪየንኮ ተናገሩ። 🟠 እስራኤል ደማስቆ በ1974 በጎላን ተራሮች የተቋቋመውን የግጭት መከላከያ ክልል ጥሳለች በማለት የሶሪያ ጦር ሰራዊት መሰረተ ልማት ላይ ጥቃት አድርሳለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik