የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ የዚምባብዌን ቀዳማዊት እመቤት ተቀብለው ለፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ግብዣ አቀረቡ

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ የዚምባብዌን ቀዳማዊት እመቤት ተቀብለው ለፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ግብዣ አቀረቡ ሉካሼንኮ የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ኦክሲሊያ ምናንጋግዋ እና የዚምባብዌ የንግድ ቡድን ተወካዮችን አግኝተው ከሀገሪቱ ጋር የተደረሱ ሁሉንም ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆኑ ገልጸዋል። "በስላቪክ ባህል ቀን (ቪቲብስክ ቤላሩስ የሚካሄደው ስላቪክ ባዛር ፌስቲቫል) ወደ እኛ በመምጣታችሁ እና ጥቂት የዚምባብዌን ባህል ይዛችሁ ስላመጣችሁልን በጣም ደስ ብሎኛል። ለእናንተ፣ ለሀገራቹ አና ፕሬዝዳንታቹ ያለንን አመለካከት ታውቃላችሁ" ሲሉ ከዚምባቡዌ ለመጡት እንግዶች መናገራቸውን የፕሬዝዳንቱ የፕሬስ ቢሮ አስታውቋል። ፕሬዝዳንቱ የዚምባብዌ መሪ ኤመርሰን ምናንጋግዋ ቤላሩስን ይጎበኛሉ ብለው እየጠበቁ መሆናቸውን ገልፀው "ለረጅም ጊዜ ጓደኛዬ ኢመርሰን መልካም ምኞቴን እና ስምምነታችንን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆንን" ግለፁ ሲሉም አክለዋል። ሉካሼንኮ የቤላሩስ የንግድ ፌስቲቫልን እየጎበኙ ከነበሩት የናይጄሪያ ቀዳማዊት እመቤት ኦሉሬሚ ቲኑቡ ጋርም እንዲሁ በተመሳሳይ ቀን ተገናኝተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik