የቤላሩስ ፕሬዝዳንት የናይጄሪያ አቻቸው ቦላ ቲኒቡ ሚንስክን ይጎበኛሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገለፁ
አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ሀገራቸው ከናይጄሪያ ጋር ትብብር ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል። የቤላሩሱ መሪ ከናይጄሪያ ቀዳማዊት እመቤት ኦሉሬሚ "ሬሚ" ቲኑቡ ጋር በሚንስክ ረቡዕ ዕለት እንደተገናኙ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት የፕሬስ አገልግሎት አስታውቋል።
"ቤላሩስ መምጣትዎ በጣም ጥሩ ነው። ለትብብራችን አስደሳች እና ጠቃሚ ጅማሮ ይሆናል። ተቀራርበን መተባበር እንድንጀምር ከእርስዎ ጉብኝት በኋላ ፕሬዝዳንቱ እና ሚኒስትሮቻቸው ቤላሩስን ይጎበኛሉ ብዬ በጣም ተስፋ አደርጋለሁ" ማለታቸውን የፕሬስ አገልግሎቱ ገልጿል።
ሉካሼንኮ አክለውም "በሀገርዎ ላይ በጣም ፍላጎት አለን፤ ለእናንተም እንጠቀማለን ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።
ሉካሼንኮ ቀዳማዊ እመቤቷ ለቦላ ቲኑብ መልካም ምኞታቸውን እንዲያደርሱም ጠይቀዋል። የቤላሩስ ፕሬዝዳንት "በማንኛውም ጊዜ ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንን ንገሯቸው" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia