የደቡብ አፍሪካ ኢነርጂ ሚኒስትር በታዳሽ ኃይል አጠቃቀም ዙርያ "ከፍተኛ" ግፊት እንደሚያደርጉ ተናገሩ
እንደ አዲስ የተቋቋመውን የኢነርጂ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የሚመሩት ክጎሲየንትሾ ራሞክጎፓ ሰኞ ዕለት ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት ቃለ መጠይቅ ለሀገሪቱ ቁልፍ የኃይል ምንጭ ከሆነው የድንጋይ ከሰል ለመሸጋገር ያላቸውን ቁርጠኝነት አፅንዖት በመስጠት ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ባለሀብቶችን ለመሳብ እና ደቡብ አፍሪካን በአፍሪካ በታዳሽ ኃይል ልማት መሪ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት በማስመር "በታዳሽ ኃይል አጠቃቀም ዙርያ ጠበቅ ያለ ግፊት አደርጋለሁ። በጣም ከፍተኛ ድርሻ ታያላችሁ" ብለዋል።
የራሞክጎፓ መግለጫ የቀድሞው አስተዳደር የድንጋይ ከሰል አጠቃቀምን በፍጥነት ለማቆም ያሳይ ከነበረው ግትርነት የተለየ አቋም ነው።
የሚኒስትሩ መግለጫ በሀገሪቱ አንጻራዊ መረጋጋት በታየበት ወቅት የመጣ ነው። ደቡብ አፍሪካ ያለ መብራት መቆራረጥ ከ100 ቀናት በላይ ያሳለፈች ሲሆን ለዓመታት ይታይ ከነበረው አክሳሪ የመብራት መቆራረጥ አንጻር አስደናቂ ስኬት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia