ቭላዲሚር ፑቲን በጥቅምት ወር በሩሲያ ካዛን ለሚካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ናሬንድራ ሞዲን ጋበዙ
በሩሲያ እና ህንድ መካከል ያለው ግንኙነት የተለየ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ እንዳለው ፑቲን ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ህንድ በተባበሩት መንግስታት፣ ብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ መድረክ ተቀራርበው እንደሚሰሩ የሩሲያው መሪ አስታውቀዋል።
በ2024 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በ20% እንደጨመረ አክለዋል።
"ከእርስዎ ጋር ያለማቋረጥ እየተገናኘን ነው፣ ዋና ትኩረታችን የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት ነው" ያሉት ፑቲን ይህ የሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ጥቅም መሆኑን አስገንዝበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia