አዲሱ የእንግሊዝ መንግስት ህገወጥ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅዱን መተዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ
አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በዳውኒንግ ስትሪት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሊሳካ የማይችል ፕሮጀክት በማለት አስረግጠው ተናግረዋል።
"የሩዋንዳ እቅድ ከመጀመሩ በፊት ሞቶ ተቀብሯል።ህገ ወጥ ፍልሰትን ለማስቆም መፍትሄ ሆኖ አያውቅም" ሲሉ ስታርመር ተናግሯል።"ሕገወጥ ስደትን ለማስቆም በማያስችሉ አሠራሮች ለመቀጠል ዝግጁ አይደለሁም።"
ቀደም ሲል በብሪታንያ እና በሩዋንዳ መንግስታት መካከል የተፈረመው ስምምነት መሠረት፣ ከሁለቱ ሀገራት በአንዱ ወገን ሥምምነቱን የማቋረጥ አማራጭን(መብትን)ያካትታል።
ወደ ብሪታንያ የሚገቡ ህገወጥ ስደተኞችን ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር መላክን የሚመለከተው ይህ እቅድ ከሁለት አመት በፊት በቦሪስ ጆንሰን መንግስት የቀረበ ቢሆንም ተተኪዎቹ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ከአውሮፓ የሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት ተቃውሞ ስለገጠማቸው ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ማድረግ አልቻሉም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩዋንዳ ባለስልጣናት 275 ሚሊዮን ዶላር ከለንደን አግኝተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia