የሱዳን የሠላም ሂደት ሁሉንም የፖለቲካ ሃይሎች ማሳተፍ አለበት ሲሉ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ።

የሱዳን የሠላም ሂደት ሁሉንም የፖለቲካ ሃይሎች ማሳተፍ አለበት ሲሉ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ። "የሱዳን ግጭት የሚፈታው በውስጥ ሃይሎች መስተጋብር እና ፍቃድ ላይ እንጂ በውጭ ጣልቃ ገብነት አለመሆኑን እርግጠኛ ነን"ሲሉ ባድር አብደል አቲ ተናግረዋል። በካይሮ በተካሄደው የሱዳን የሲቪል ፖለቲካ ቡድኖች ስብሰባ"መንግስታዊ ተቋማትን መጠበቅ ለሱዳን ሉዓላዊ ህልውና ዋስትና መሆን አለበት"ሲሉ አሳስበዋል።ከዚሁ ጎን ለጎን የሱዳን ታጣቂ ሃይሎች አንድነት ለሀገሪቱ መከላከያ ወሳኝ እንደሚሆን ጠቁመዋል። የግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካይሮ በግጭቱ ውስጥ ካሉት ወገኖች ጋር ግንኙነት ማድረጉን እንደሞትቀጥል እና በሱዳን ያለውን የትጥቅ ግጭት በፍጥነት ለማስቆም ከአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ጋር በንቃት እየሰራች መሆኑን አረጋግጠዋል። ቀውሱን ለማስቆም እና ለሱዳን ህዝብ አፋጣኝ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ እንዲሁም የአለም አቀፉ ማህበረሰብን የሰላም እርምጃዎች ለመደገፍ አስቸኳይ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠይቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik