"መቀላቀል ወይ መሞት": የአሜሪካ ዜጎች በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ውስጥ ተገድደው እንደገቡ ተናገሩ።
በግንቦት ወር መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል በሚል ሁለት የአሜሪካ ዜጎች በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
እ.አ.አ ግንቦት 19፣ የታጠቁ ሰዎች በኪንሻሳ የሚገኘውን የፕሬዚዳንቱን ቢሮ ለአጭር ጊዜ በመያዝ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማድረጋቸውን እና ክርስቲያን ማላንጋ የተባለው መሪ በጸጥታ ሃይሎች መገደሉ ይታወሳል።
የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ልጅ የሆነው ማርሴል ማላንጋ ለአካባቢው ቋንቋ እና ለሀገሩ እንግዳ መሆኑን በመግለጽ “አባቴ የእርሱን ትዕዛዝ ካልተከተልን እንደሚገድለን አስፈራርቶን ነበር ብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia