“አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት”፦ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስኬትና የብሪክስ ሚና የተናገሩት

“አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት”፦ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስኬትና የብሪክስ ሚና የተናገሩት የዕድገት ስኬት ታሪኮች ከአፍሪካ የሚነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ "አንጸባራቂ የብልጽግና ምልክት" ሆና ተለይታ ትወጣላች፤ ሀገሪቱ ወደ ብሪክስ ቡድን መቀላቀሏም ዘርፈ ብዙ ዓለም አቀፍ አጋርነቷን የሚያሳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር የፊስካል ፖሊሲና የመንግስት ፋይናንስ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ ቶሊና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። "ኢትዮጵያ ወደ ብሪክስ ይዛ የምትመጣው የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት እድል እንዲሁም ከአባልነቷ የምታገኘው ጥቅም በጣም ከፍተኛ ነው ብዬ አስባለሁ። ይህ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስፋትና አቅም የሚያሳይ ጉልህ ምልክት ነው ብለን እናምናለን። እስካሁን ያሳካነውን እና በአጠቃላይ ልናሳካው ለምንችለው ነገር ማስረጃ ነው። ስለዚህ በብሪክስ ስብስብ ውስጥ በንቃት እየተሳተፍን እንገኛለን" ብለዋል። ኢትዮጵያ ከበርካታ የዓለም ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት እና የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ህብረት አባል መሆኗንም አክለዋል። ይህ ታሪካዊ መሰረት እና አሁን ያለው አቅም ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ ለምትጫወተው ሚና በጥሩ አቋም ላይ እንድትሆን ያደርጋታል ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik