ሴራሊዮን ያለዕድሜ ጋብቻን የሚከለክል ህግ አወጣች

ሴራሊዮን ያለዕድሜ ጋብቻን የሚከለክል ህግ አወጣች ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ አንድ ሶስተኛ ሴት ልጆች 18 ዓመት ሳይሞላቸው በሚዳሩባት ሴራሊዮን ያለ እድሜ ጋብቻን የሚከለክል እርምጃ አፅድቀዋል። በለጋ ዕድሜ ልጅ መውለድ በሚፈጥረው አካላዊ ስጋት ምክንያት ያለዕድሜ ጋብቻ ያረገዙ ሴቶችን ሞት እንዲጨምር እንደሚያደርግ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በአዲሱ ህግ መሰረት ከ18 ዓመት በታች የሆነች ሴት ያገባ ወንድ ቢያንስ 15 አመት እስራት እና 4,000 ዶላር መቀጮ ይቀጣል። ወላጆች ወይም እንደዚህ ባሉ የጋብቻ ሥነ ሥርዓቶች ላይ የተገኙ ሰዎችም መቀጮ ይደርስባቸዋል፡፡ የዩኒሴፍ መረጃ እንደሚያሳየው በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ወደ 60 ሚልዮን የሚሆኑ ያገቡ ህጻናት የሚገኙ ሲሆን ይህም በዓለም ከፍተኛው ቁጥር ነው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik