ኢትዮጵያ ከሮሳቶም ጋር በመሰረተ ልማት ግንባታ ዙርያ ያደረገችው ስምምነት የኒውክሌር ሀይልን ለመጠቀም ትልቅ ዕርምጃ ነው ሲሉ የቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ስምምነቱ የተደረሰው እ.አ.አ ሐምሌ 2023 በተካሄደው 2ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ነበር።
ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ ከቻይና የልዑካን ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከሩሲያ መንግስት የኒውክሌር ኩባንያ ጋር ያለው ትብብር ለአፍሪካዊቷ ሀገር የልማት ግቦች ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል።
የቻይና ብሔራዊ የኒውክሌር ኮርፖሬሽን ተወካዮች ከኢትዮጵያው ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው በኒውክሌር ሀይል ዘርፍ የመሰረተ ልማት እና የሰው ሃይል ልማት ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia