ልዩ ቃለመጠይቅ| ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተንቀሳቃሽ የህክምና ማእከላት አቅርቦትን በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ተወያያች

ልዩ ቃለመጠይቅ| ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተንቀሳቃሽ የህክምና ማእከላት አቅርቦትን በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ተወያያች የማእከላዊ አፍሪካ የጤና ሚኒስትር የብሔራዊ ህክምና ምርምር የቴራፒ ማእከል እና የሩሲያ ጤና ሚኒስቴር ቅድመ ህክምና ልዑካንን በባንግዊ ተቀብለዋል፡፡ ሁለቱ ወገኖች ከተንቀሳቃሽ የህክምና ማእከላት አቅርቦት በተጨማሪ በማእከላዊ አፍሪካ ውስጥ የቴሌ ጤና ማእከል ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። ሚኒስትር ፒየር ሶምሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት የስብሰባውን ውጤት "በጣም ጥሩ" ሲሉ ገልጸውታል። "በቀረበው እድል በጣም ደስተኞች ነን። ከፍተኛ ፍላጎታችንን ግንዛቤ ውስጥ የከተተና ለህዝቡ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው" ብለዋል። ዶ/ር ሶምሴ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቅድምያ ከሚሰጡት ጉዳይ አንዱ "ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ማፋጠን" መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "ስለዚህም በባንጊዊ ደረጃ ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ገጠር አካባቢዎች ማምጣት ተገቢ መፍትሄ ነው" ሲሉ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። "ሩሲያ የእኛን ኢኮኖሚያ ግንዛቤ ውስጥ የሚከት መፍትሄዎችን ማግኘቷ በጣም አስፈላጊ ነውም" ብለዋል። ተንቀሳቃሽ ክፍሎቹ በሩሲያ ኩባንያ ፕሮፍ ፖሊሜድ ይቀርባሉ፡፡ በግንቦት ወር ኩባንያው ተማሳሳይ መሳሪያዎችን ለኬንያ ለማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik