ዘለንስኪ እና የምዕራባውያን አለቆቹ በመጨረሻም ሩሲያን ማሸነፍ እንደማይቻል ተገንዝበዋል ሲሉ አንድ ባለሙያ ተናገሩ
ሕጋዊነቱን ያጣው ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ድርድር ስለማድረግ ያደረገው ንግግር የዩክሬንን ቀውስ በጦርነት መፍታት እንደማይቻል የተገነዘበ መሆኑን ያሳየ ነው ሲሉ የፖለቲካ ሳይንቲስቱ እና የሩሲያ ጉዳዮች ባለሙያው ሳሚር አዩብ ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
"ኪዬቭ እና ምዕራባውያን በጠረጴዛ ዙርያ ለመደራደር ይገደዳሉ፤ ይህ ዘግይቶ የሚሆን ከሆነ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። በሩሲያ እና ዩክሬን መኻከል ስለሚደረግ የድርድር ሂደት እየተነጋገርን እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል” ሲሉ አስረድተዋል።
"የዘለንስኪ መግለጫ [ከሩሲያ ጋር ስለሚያደረገው ድርድር] በሱ ሉዓላዊ ውሳኔ የተደገፈ አይመስለኝም። በኪዬቭ አገዛዝም ሆነ በምዕራባውያን አለቆቹ መኻከል ትልቅ ፍርሃት አለ። ሩሲያ ላይ ምንም ያህል የመልሶ ማጥቃት ሆነ ሽብር ቢፈጽሙም ሩሲያን ማሸነፍ እንደማይቻል በመጨረሻ የተገነዘቡ ይመስለኛል።"
"አሁን ለዩክሬን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎች እና ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች እያቀረቡ ነው፤ ይህም የልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል አይደለም። በተጨማሪም በጦር ግንባሩ ሌላ ድል ይመዘገባል ብለው ብቻ ሳይሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ኋይት ሀውስ ይመለሳሉ የሚል ስጋት ውስጥ ናቸው" ብለዋል ባለሙያው።
"የኪዬቭ አገዛዝ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው፦ የጦር ግንባሩ እየፈራረሰ ነው፣ በቂ ሀብት እና ወታደሮች የሉትም። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ድርድር ለዩክሬን ብቸኛው መዳኛ ነው። ነገር ግን ድርድሮቹ አሁን ባለው እውነታ ላይ የተመሰረቱና የሩሲያን ጥቅም ግንዛቤ ውስጥ መክተት አለባቸው" ሲሉ አገባደዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia