ሩሲያ በ2024 ከ200,000 ቶን በላይ እህል ወደ ሞሮኮ ልካለች

ሩሲያ በ2024 ከ200,000 ቶን በላይ እህል ወደ ሞሮኮ ልካለች የሞሮኮ ልዑካንን የተቀበለው የሩሲያ የግብርና ተቆጣጣሪ አካል አብዛኛው ስንዴ እንደሆነ አስታውቋል። ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ በሰሜን ምዕራብ ሩሲያ የሚገኘው የቪሶትስክ ወደብ ብቻ 94,000 ቶን እህል ወደ ሞሮኮ መላኩን ተቆጣጣሪው አካል ሮሴልኮዝናድዞር ተናግሯል። የሞሮኮ የልዑክ ቡድን በሩሲያ ጉብኝቱ የጥራት ቁጥጥር እና የጭነት ደህንነትን የሚያካትተውን ሂደት ለመከታተል ችሏል። ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ ትብብር በተለይ በኤክስፖርት ዙርያ እንዲሁም የሩሲያው ተቆጣጣሪ አካል የመረጃ ስርዓትን የተመለከተ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል። የፀረ-ተባይ እና የግብርና ኬሚካሎች አያያዝን አስመልክቶ የመግባቢያ ሰነድ መፈረም በሚቻልበት መንገድ ላይም ተወያይተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik