በኒው ካሌዶኒያ ተቃዋሚ ሰለፈኞች ከድምፅ መስጫ ጣቢያ ውጪ መኪና አቃጥለዋል፤ የመጀመሪያውን ዙር የህግ አውጭ ምክር ቤት ምርጫንም አስተጓጉለዋል።
ከዚህም በላይ በከባድ የኮንክሪት ብሎክ እና የዛፍ ቅርንጫፎች በመግቢያው ዘግተው እንደነበር የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በግንቦት ወር የማክሮን ፓርቲ በአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ሽንፈት ማካጠውን ተከትሎ በማክሮን የተበተነውን ብሄራዊ ምክር ቤት ምርጫ ለመምረጥ የመጀመሪያው ዙር ምርጫ በዛሬ እለት እየተካሄደ ይገኛል።
በደቡብ ምእራብ ፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው የፈረንሳይ ደሴት ፤ ኒው ካሌዶኒያ እ.አ.አ ከግንቦት 13 ጀምሮ በተነሳ ሁከት፤ማክሮን በግዛቲቱ የድምጽ መስጠቱን ሂደት ለጊዜው እንዲቆም አድርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia