የሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች
🟠 የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲን የመካከለኛ እና የአጭር ርቀት የመሬት ላይ ሚሳኤሎችን መዘርጋትን በተመለከተ ከሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ጋር ተወያይተዋል።
🟠 የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የአሜሪካ ሰራሹን MLRS ሮኬት በሩሲያ ሰራሹ ኢስካንደር ሚሳኤል ተመቶ ሲወድም የሚያሳይ ቪዲዮ አሳይቷል።
🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ያልተሳካ ክርክር ካደረጉ በኋላ ከምርጫው ውድድር ራሳቸውን አያገለሉም ሲሉ የዘመቻው ተወካይ ተናግረዋል።
🟠 የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት አሊዬቭ ፓርላማውን በትነው እ.አ.አ ለመስከረም 1 አስቸኳይ ምርጫ እንዲደረግ ወስነዋል።
🟠 የፈረንሳይ ባለስልጣናት በኒው ካሌዶኒያ ተነስቶ በነበረው አለመረጋጋት ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ እሰከ እ.አ.አ እስከ ሐምሌ 8 ድረስ አራዝመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia