ኢኮዋስ ሽብረተኝነት ለመዋጋት 5,000 አባላት ያሉት የጸጥታ ሃይል ለማደራጀት በዓመት እስከ 2.6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገዋል ተባለ።
የናይጄሪያ መከላከያ ሚኒስትር መሐመድ ባዳሩ አቡበከር በኢኮዋስ (ECOWAS )የመከላከያ እና የገንዘብ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት፤ ኢኮዋስ ሁለት አወቃቀሮች አማራጮች እንዳሉት አንስተዋል።አንደኛው አማራጭ 5,000 ብርጌድ በዓመት 2.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልገው ጦር መገንባት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 1,500 ወታደሮችን የሚይዝና በዓመት 481 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚያስፈልገው ጦር መገንባት መሆኑን ተናግረዋል።
አቡበከር "እነዚህ አሃዞች ከፊታችን ያለውን ተግባር ከባድነት ያሳያሉ" ብሏል። "በመሆኑም አካባቢያችን ላይ እያጋጠሙ ያሉትን ወቅታዊ ተግዳሮቶች እና የአባል ሀገራት የፋይናንስ ችግሮች ግምት ውስጥ በማስገባት አማራጮችን በጥልቀት መገምገም አስፈላጊ ነው" ሲሉም በመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
አቡበከር አክለው የኢኮዋስ ሃይል የሚኖረው ስልጣን ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ላይ ብቻ የሚወሰን መሆኑን ጠቁመው፣ እያንዳንዱ አባል ሀገር የሚወሰንበት ኮታ እንደሚኖር ተናግዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia