ማሊ በቡጉኒ ማዕድን ማውጫ በሚደረገው የሊቲየም ማምረት ሥራ የኢንዱስትሪ ቁልፍ ተዋናይ ለመሆን ተዘጋጅታለች።
እ.አ.አ በ2024 መገባደጃ ላይ ምርት የሚጀምር ሲሆን፣ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ክምችት ተገኝቷል።
ፕሮጀክቱን የሚቆጣጠረው ኮዳል ሚኒራልስ የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ተስፋ ሰጪ የቁፋሮ ውጤቶች መኖራቸውን አስታውቋል። የከባድ ፈሳሽ ማብለያ ፋብሪካው የአገልግሎት ዘመን በአራት ዓመታት ሊራዘም ይችላል፣ ይህም እ.አ.አ በ2024 እና 2036 ባለው ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ የስፖዱሜኔን ምርት ወደ 585,000 ቶን ያሳድጋል።
በመጀመሪያ ለአራት አመታት በዓመት 125,000 ቶን ለማምረት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፥ እ.አ.አ ከ2026 ጀምሮ በዓመት 230,000 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የኮዳል ማዕድናት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት በርናርድ አይልዋርድ "በቡጉኒ ሊቲየም ፕሮጀክት ላይ ያለው ተስፋ ከምንጠብቀው በላይ ነው እናም እነዚህ አዳዲስ፣ሰፊ እና ከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ የፔግማቲት ሚኒራላይዜሽን ቀጣይነት እንዳሚኖራቸው ፍንጭ ይሰጣሉ" ብለዋል።
ተጨማሪ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች በተመሳሳይ ማዕድን ማውጫ እስከ 1.74% ሊቲየም ማዕድን ውጤቶች እንዳለ እና ይህ ከተጠበቀው በላይ መሆኑ ተነግሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia