በኬንያ የታክስ ጭማሪን በመቃወም በተቀሰቀሰ ሁከት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 17 ያህሉ ደግሞ መቁሰላቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል።
ረቡዕ ዕለት በነበረው ተቃውሞ ሰልፉ 23 ሰዎች መሞታቸውንና 50 የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በምዕራባዊቷ ሮንጋይ ከተማ ሰልፈኞች ሱፐርማርኬቶችን መዝረፋቸው እና ሁለት ተጨማሪ ሰዎች መሞታቸውን ዘ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል።
በምዕራብ ኬንያ በሞትገኘው ሆማ ቤይ ካውንቲ፣ ስምንት ህጻናትን ጨምሮ 11 ሰዎች ቆስለዋል ሲል የኬንያው ኤን ቲቪ ቻናል ዘግቧል። አንድ ሐኪም በቀጥታ ሥርጭት ላይ ገብቶ እንደገለፀው፤ ስምንት ታካሚዎችን ሆስፒታል መግባታቸውን እና ሁሉም በጥይት ተመትተው መቁሰላቸውን ተናግሯል።
በአጎራባች ሚጎሪ ካውንቲ፣ ተቃዋሚ ስልፈኞች ከፖሊስ ጋር በመጋጨታቸው ሳቢያ 6 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።
በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢም ግጭት መቀጠሉንና ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን ረፋዱ ላይ አስለቃሽ ጭስ በመተኮሱ ህዝቡን መበተኑን ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia