የኮንጎ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በስዊዘርላንድ የተካሄደውን የዩክሬን ጉባኤ"ትርጉም የለሽ" ሲሉ አጣጣሉ።
በዩክሬን ግጭት ዙሪያ በስዊዘርላንድ የተካሄደው ስብሰባ ያለ ሩሲያ ተሳትፎ መደረጉ ከንቱ ነው ፤ ከዚህ ስብስብ ምንም ነገር ፍሬ ነገር አይገኝም ሲሉ የኮንጎ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን ክላውድ ጋኮሶ ለሩሲያ ቴሌቪዥን አስታውቀዋል።
እኛ መሳተፍ አልፈለግንም ምክንያቱም እውነት ስለ ሰላም ከሆነ ሁለቱም ወገኖች መገኘት አለባቸው ብለን ስለምናምን ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።"ሩሲያ በዚያ ስብሰባ እንደማትገኝ ስናውቅ፣ ስብሰባው እርባና ቢስ መሆኑን ተረድተናል።ከዚህ ስብስብ ምንም ፍሬ ነገር አይጠበቅም።"
ቀደም ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የኮንጎ አቻቸው የዩክሬን ቀውስ እና የብዙሃ ዋልታ አለምን ስርዓት ማስተዋወቅን ጨምሮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በሌሎች መድረኮች ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ ውይይቶችን ለማጠናከር እና የቅርብ ቅንጅቶችን ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia