በምዕራብ ኒጀር በደረሰ የሽብር ጥቃት 21 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል።
የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የሀገሪቱ የዜና ወኪል እንደዘገበው በታሲያ መንደር አቅራቢያ “ በታጠቁ የአሸባሪ ቡድኖች ጥምረት” በፀጥታ ሃይሎች ላይ ባደረሰው ጥቃት 20 ወታደሮች እና አንድ ግለሰብ ፣ በድምሩ 21 ሰዎች ተገድለዋል።
በጥቃቱ ዘጠኝ ወታደሮች መቁሰላቸውን እና በሁለት የሰራዊቱ መኪኖች ላይ ጉዳት መድረሱን መግለጫው ገልጿል።
በሪፖርቱ መሰረት ተሽከርካሪዎቹ እና የመገናኛ መሳሪያዎቹ ሲወድሙ፣12 የሚሆኑ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት ተገድለዋል። በተጨማሪም የአየር እና የመሬት አሰሳ በማጠናከር የቀሩትን የአሸባሪው ቡድን አባላት ለማጥፋት ተሰማርተዋል።
የኒዠር ባለስልጣናት ከረቡዕ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሀዘን አውጀዋል፣ በዚህ ጊዜ የሞቱ ወታደሮችን በማስታወስ የሀገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲሰቀል ይደረጋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia